Telegram Group & Telegram Channel
የፍቅር ቃጠሎ

ጉንጭሽ ፅጌረዳ ሞቆት የፈነዳ
ዐይንሽ የጠዋት ጨረር የበራ ማለዳ፡፡
የማትጠገቢ የስንዴ ራስ ዛላ አገዳ ጥንቅሽ
ጠብ አትይ አንጀቴ ባኝክ ብመጥሽ፡፡
ቆንጆ ነሽ አንቺዬ እሳት ነበልባል ነሽ ንዳድ ባከላቴ
ሆነሻል ሙቀቴ ሆነሻል ህይወቴ፡፡
የጋለው ትንፋሽሽ
የሞቀው ምላስሽ
ማርኮኝ በከንፈርሽ
እጄን ሰጥቻለሁ
እስረኛ ሆኛለሁ፡፡
ያንቀጠቅጠኛል ወባ ቅናት ገብቶ
ልቤን አስፈራርቶ
ትኩሳት አምጥቶ፡፡
ፍቅርሽ አቃጠለኝ በመልክሽ ልተክዝ
እቀፊኝ ልቀዝቅዝ
ንከሺኝ ልደንዝዝ፡፡

✍️✍️ገብረክርስቶስ ደስታ

@loret_tsegaye
@loret_tsegaye



tg-me.com/loret_tsegaye/2586
Create:
Last Update:

የፍቅር ቃጠሎ

ጉንጭሽ ፅጌረዳ ሞቆት የፈነዳ
ዐይንሽ የጠዋት ጨረር የበራ ማለዳ፡፡
የማትጠገቢ የስንዴ ራስ ዛላ አገዳ ጥንቅሽ
ጠብ አትይ አንጀቴ ባኝክ ብመጥሽ፡፡
ቆንጆ ነሽ አንቺዬ እሳት ነበልባል ነሽ ንዳድ ባከላቴ
ሆነሻል ሙቀቴ ሆነሻል ህይወቴ፡፡
የጋለው ትንፋሽሽ
የሞቀው ምላስሽ
ማርኮኝ በከንፈርሽ
እጄን ሰጥቻለሁ
እስረኛ ሆኛለሁ፡፡
ያንቀጠቅጠኛል ወባ ቅናት ገብቶ
ልቤን አስፈራርቶ
ትኩሳት አምጥቶ፡፡
ፍቅርሽ አቃጠለኝ በመልክሽ ልተክዝ
እቀፊኝ ልቀዝቅዝ
ንከሺኝ ልደንዝዝ፡፡

✍️✍️ገብረክርስቶስ ደስታ

@loret_tsegaye
@loret_tsegaye

BY ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን እና ሌሎችም


Warning: Undefined variable $i in /var/www/tg-me/post.php on line 280

Share with your friend now:
tg-me.com/loret_tsegaye/2586

View MORE
Open in Telegram


ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን እና ሌሎችም Telegram | DID YOU KNOW?

Date: |

A project of our size needs at least a few hundred million dollars per year to keep going,” Mr. Durov wrote in his public channel on Telegram late last year. “While doing that, we will remain independent and stay true to our values, redefining how a tech company should operate.

ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን እና ሌሎችም from us


Telegram ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን እና ሌሎችም
FROM USA